(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታተል ቡድን “በመልካም ሥነምግባር የታነፀ፣ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ገላን ልዩ የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ አካሄደ።
የክፍለ ከተማው የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ አቶ ደሴ አባተ በት/ቤቱ ተገኝተው ሙስናን የሚፀየፍ፣ በመልካም ሥነምግባር የታነፀ፣ ሀገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠር ላይ የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተማሪዎች በት/ቤታቸው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ በማቋቋም መልካም ሥነምግባር የተላበሰ እና ለሌሎች አርዓያ በመሆን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ፅንሰ ሀሳቡንና አላማን ከግብ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡
በተያያዘም በሥነምግባር የታነፁ፣ መምህራንና ወላጅ የሚካብር፣ የማህበረሰቡን ጠቃሚ እሴት ጠብቆ የሚያስቀጥል፣ ብልሹ አሰራንና ሌብነትን የሚፀየፍ ትውልድ ለማፍራት በትምህርት ቤት ማህበረሰብ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር አላማ ያደረገ ንቅናቄ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም ተማሪዎች በራሳቸው የሚተማመኑ ኩረጃን የሚፀየፍና በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
በመጨረሻም ተማሪዎች በራሳቸው የሚተማመኑ ኩረጃን የሚፀየፍና በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
+ There are no comments
Add yours