ምክር ቤቱ 3 ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ ሶስት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን እና የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ስርዓት ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ለዝርዝ እይታ ወደሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል::

በምክር ቤቱ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚንስቴር ዴኤታ የተከበሩ ወ/ሮ መሰረት ሀይሌ ረቂቅ አዋጆቹን አስመልክቶ አጭር ማብራሪያ ያቀርቡ ሲሆን፤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ዓላማ የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ ወይም ለመውረስ እንዲሁም ለማስተዳደር የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ረቂቁ ማንኛውም ሰው በህገ ወጥ ድርጊት ጥቅም እንዳያገኝ ለማድረግ የሚያስችል የንብረት ማስመለስና ማስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል መጠቆሙን ከምክር ቤቱ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

You May Also Like

More From Author

+ There are no comments

Add yours