6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

Directorates

Public and International Relations / የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ትምህርቶችን/መልዕክቶችን ማዘጋጀት፣
 • የፊት ለፊት ግንኙነትን፣ የህትመት ወጤቶችን፣ የኤሌክትሮኒክና ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ተደራሽ ማድረግ፣
 • የውስጥና የዓለም አቀፍ ግንኙነትን በማጠናከር የኮሚሽኑን ገጽታ መገንባት፣
 • በዘርፉ የበላይ አመራርንና የሥራ ክፍሎችን ማማከር፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣ የፈጻሚዎችን የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣
 • የድጋፍ፣ ክትትል እና ግምገማ ሥራዎችን መስራት፤
 • በዚህም ግንዛቤው ያደገና ሙስናን መታገል የሚችል ህብረተሰብ በመፍጠር የኮሚሽኑን ተልእኮ ማሳካት ነው፡፡

Ethics Liaison and Corruption Prevention / የሥነምግባር መከታተያና ሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • በተቋማት (መንግስት መሥሪያ ቤት፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች፣ ህዝባዊ ድርጅቶች እና ዩኒቨርስቲዎች) የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጅና የመፈጸም አቅማቸው እንዲጎለብት ማድረግ፣
 • በተቋማት የሥነምግባር ኮድ፣ የተቋናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ እና የአሰራር ሥርዓት ጥናት ማሻሻያ ሀሳቦችን ማስተግበር፣
 • በዩኒቨርስቲዎችና የሙያና ቴክኒክ ተቋማት ውስጥ የህፃናትና ወጣቶች ሥነምግባር ግንባታ ሥራ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣
 • አዳዲስ አሰራሮችን መዘርጋት፣ የፈፃሚዎች የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣ መከታተል፤
 • በዚህም የህዝብና የመንግስት ሃብትን ከሙስና ማዳንና ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት በመከላከል የዳይሬክቶሬቱንና የኮሚሽኑን ተልዕኮ ማሳካት ነው፡፡

Ethics building and Public Participation Coordination / የሥነምግባር ግንባታና ሕብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 

Training Study and Research / የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን የመፈጸም አቅም የሚያጎለብቱና ለፀረ ሙስና ትግል ውጤታማነት የሚያግዙ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን መሥራት፣
 • የአስተምህሮ ማቴሪያሎችን ማዘጋጀት፣ እንዲዘጋጅ ማድረግና አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረግ፣
 • የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ትምህርቶችና ስልጠናዎችን መስጠት፣እንዲሰጥ ማድረግ፣ የፈፀሚዎች የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣
 • አዳዲስ አሰራሮች መዘርጋት፣ ክትትልና ድጋፍ ማካሄድ፣
 • በዚህም በሥነምግባር የተገነባና ሙስናን የሚታገልና የሚጠየፍ ህብረተሰብ በመፍጠር የዳይሬክቶሬቱንና የኮሚሽኑን ተልዕኮ ማሳካት ነው፡፡

Asset Disclosure and Registration / የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • በህግ ሀብትና ጥቅማቸውን ማሳወቅና ማስመዘገብ የሚገባቸውን ተመረጮች፣ ተሿሚዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ሠራተኞችን ዝርዝር መረጃ መያዝ፣
 • ሀብትና ጥቅማቸውን እንዲያሰውቁና እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፣
 • የተመዘገበ ሀብት መረጃዎችን ማስተዳደር፣
 • የሀብት አስመዘገቢዎች መረጃ ተገቢነት ባለው ቴክኖሎጂ ለህዝብ ከፍት ማድረግ፣
 • የሀብት አስመዝገቢዎች መረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣
 • የከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ሥነምግባር ደንብ ማዘጋጀት፣ ማሻሻል፣ አፈፃፀም መከታተል፣ የጥቅም ግጭት መከላከል፣ ማስተዳደር፣
 • አዳዲስ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ የፈፃሚዎች የመፈፀም አቅም ማሳደግ፤
 • በዚህም በመንግስት አገልግሎት አሠጣጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት አሠራርን በማስፋፋት የዳይሬክቶሬቱንና የኮሚሽኑን ተልዕኮ ማሳካት ነው፡፡

Anti-Corruption legal Advice Implementation and Experience Formulation / የፀረ-ሙስና ሕግ ምክር፣ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን የበላይ አመራርና ዳይሬክቶሬቶች ማማከር፣
 • የኮሚሽኑ ህግ፣ ደንብ፣ መመሪያና ማኑዋሎችን ከተልዕኮው አንፃር በመቃኘት ማውጣት፣
 • የሀገሪቱን የፀረ ሙስና ህጎች መከበራቸውን መከታተልና ማማከር፣
 • ሀገሪቱ የተቀበለቻቸውን የፀረ-ሙስና ትግል ኮንቬንሽኖች ማስተግበር፣ 
 • በሀገር ህግና ፖሊሲ መሠረት ዓለም አቀፍ ትብብርን ማስፈጸም፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣ የፈፃሚዎችን የመፈፀም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የሀገሪቱ የፀረ ሙስና ህጎችና የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን ተግባራዊነትና ውጤታማነትን ማረጋገጥና ማገዝ ነው፡፡

Regional Affairs Coordination / የክልል ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይረክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የፌዴራልና የክልል ኮሚሽኖች ሀገራዊ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣መከታተል፣ ማስገምገም፣ አፈፃፀም ሪፖርት ማዘጋጀት ማሳተምና ማሠራጨት፣
 • የክልል ኮሚሽኖችን የመፈጸም አቅም ክፍተቶቻቸውን በመለየት የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎችን መሥራት፣
 • የክልል የፀረ ሙስና ጥምረቶችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲደራጁና እንዲሟሉ፣ በፀረ ሙስና ትግሉ በንቃትና በትጋት እንዲሳተፉና ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ፣
 • የተማሪዎች የሥነምግባር ማጎልበቻ ስትራቴጂን እንዲተገበር ክትትል ማድረግ፣
 • የክልል ተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጅና የመፈጸም አቅማቸው እንዲጎለብት መደገፍና መከታተል፣
 • በህግ ሀብትና ጥቅማቸውን ማሳወቅና ማስመዘገብ የሚገባቸውን የክልል ተመረጮች፣ ተሿሚዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ እንዲያዝ፣ ሀብትና ጥቅማቸውን እንዲያሳውቁና እንዲያስመዘግቡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 • የሀገሪቱን የፀረ ሙስና ህጎች በክልሎች መከበራቸውን መከታተል፣ መደገፍ፣
 • ክልሎች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ትምህርቶችን/መልዕክቶችን ማዘጋጀታቸውን፣ የህትመት ወጤቶችን፣ የኤሌክትሮኒክና ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጠቅመው ተደራሽ እንዲያደርጉ መደገፍ፣መከታተል፣ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዝገቡትን በመለየት እንዲበረታቱ ማድረግ፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣  የፈፃሚዎችን የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣ ክትትል ማድረግ፤
 • በዚህም የሀገሪቱ የመልካም ሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራን ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡

Change Management and Capacity Building / የለውጥ ሥራ አመራርና አቅም ግንባታ ዳይረክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን የለውጥ ትግበራንና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አፈጻጸሞችን መከታተልና ማስቀጠል፣
 • የአመራርና ሠራተኞችን የመፈጸም አቅም ክፍተት ላይ የተመሰረተ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና መስጠት፣
 • የሥነምግባር መከታተያ ሥራን በኮሚሽኑ ተግባራዊ ማድረግ፣
 • የተገልጋይ ቅሬታና አቤቱታ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ፣
 • አዳዲስ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት፣ የፈፃሚዎች የመፈፀም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የዳይሬክቶሬቱን ተልዕኮ በማሳከት የኮሚሽኑ ተልዕኮና ራዕይ እንዲሰካ ማገዝ ነው።

Plan and Budget Administration / የዕቅድና በጀት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲዘጋጅ ማስተባበር፣ ከስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ማስረጽ፣ ዳይሬክቶሬቶች እንዲያወርዱ ማድረግ፣
 • ከሥራ ከዕቅድ ጋር የተጣጣመ የበጀት እቅድ ማዘጋጀት፣ ማስተዳደር፣ መከታተል፣ መገምገም፣ ፕሮግራም ወይም ፕሮጀክት ሰነድ በማዘጋጀት ከለጋሽ አካላት በጀት ማስገኘት፣
 • የብድር በጀት ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት ፕሮግራም ወይም ፕሮጀክት አፈፃፀም ከሙስና የፀዳ መሆኑን መከታተል፣ ሪፖርት ማዘጋጀት፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፡ የፈፃሚ የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የኮሚሽኑ በጀት በቁጠባ፣ በቅልጥፍናና ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የኮሚሽኑ አፈፃፀም ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡

Human Resource Administration / የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቱ

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑ የሰው ሀብት ዕቅድ ማቀድ፣ ማሟላት፣
 • የሠራተኛውን የሥራ ደህንነትና ጥቅማ ጥቅሞችን ማስከበር፣
 • የሰው ሀብት መረጃዎችን መያዝና ማስተዳደር፣
 • የማህደርና ሪከርድ አገልግሎት መስጠት፣
 • የሥራ ባህል፣ እሴቶችና ሥነምግባር እንዲዳብር ማድረግ፣ከሥራ መዘርዝር ጋር በተሳሰረ ሁኔታ እንዲመዘን መከታተል፣
 • በሰው ሀብት የተፈለገው ውጤት ስለመገኘቱ ኦዲት እንዲደረግ ማድረግ፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣ የፈፃሚ የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የኮሚሽኑ የሰው ሀብት ውጤታማ መሆኑን በማረጋገጥ የኮሚሽኑ ተልዕኮ እንዲሳከ ማገዝ ነው፡፡

Procurement, Finance and Property Administration / የግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን የፋይናንስ እንቅስቃሴን መምራት፣ ማስተዳደር፣ ማማከር፣
 • ግዥን መምራት፣ አቅርቦቶችን ማሟላት፣
 • ንብረት ማስተዳደር፣
 • ሂሳብና ንብረት ማስመርመር፣
 • አዳዲስ አሠራር መዘርጋት፣
 • የፈፃሚ የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የኮሚሽኑን በጀትና ንብረት በቅልጥፍና፣ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እና በቁጠባ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ ነው ፡፡

Information Communication Technology / የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን መከታተል፣ ግንዛቤ መፍጠር፣ ማስተዳደር፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣
 • የፈፃሚ የመፈፀም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የኮሚሽን አገልግሎት አሠጣጥ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ማገዝ ነው፡፡

Internal Audit / የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የውስጥ የቁጥጥር ሥርዓትን ብቃት በመገምገም የሀብት አጠቃቀምና የሥራ አፈጻጸም ውጤታማ እንዲሆን በማድረግና ተጨማሪ እሴት በመፍጠር ተቋሙ ያስቀመጣቸውን አላማዎች እንዲያሳካ እገዛ ማድረግ ነው፡፡

Women and Children Affairs / የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑን ሴቶች እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የመፈጸም አቅማቸውን ማጎልበት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣
 • የዳይሬክቶሬቱን ፈፃሚ የመፈፀም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም የኮሚሽኑን የሴቶች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡

General Services / የጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

Activities / እንቅስቃሴዎች

 • የኮሚሽኑ የትራንሰፖርት ስምሪትና ጥገና አገልግሎት ማቀላጠፍ፣
 • የቢሮ፣ የአዳራሽ፣ የምድረ ግቢ ውበት፣ ጽዳትና የጥገና እና የግቢ ደህንነት አገልግሎት መስጠት፣
 • የኮሚሽኑን አመራሮችና ሠራተኞች መኖሪያ ቤቶችን ማስተዳደር፣
 • አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣
 • የዳይሬክቶሬቱን ፈፃሚዎች የመፈፀም አቅም ማሳደግ፣
 • በዚህም ኮሚሽኑን ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ማገዝ ነው፡፡