የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች በሰንዳፉ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በተሰጠው ስልጠና ላበረከተው የላቀ አስተዋፆ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።
በመዝጊያ መርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በእውቀትና በአመለካከት የታነፀ የሰው ኃይልና ግብዓት የተሟላ ዘመናዊ የሕግ አስከባሪ ተቋማት ሊኖራት ይገባል ብለዋል።
ስልጠናው የመሬት ወረራን አና ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎችና ከሥራ ባህሪው አኳያ የሚስተዋሉ የብልሹ አሰራር ችግሮችን በመከላከልና በመቆጣጠር የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ በብቃት ላይ የተመሰረተ ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊድያ አክለውም የወሰዳችሁትን ስልጠና እንደተጨማሪ አቅም በመጠቀምና ከማንኛውም የሥነምግባርና የብልሹ አሰራር ችግር ነፃ በመሆን ከተማዋ ያስቀመጠችውን ራዕይ በሕዝብ ተሳትፎ ሰላምና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት አለባችሁ ብለዋል።
በተሰጠው ስልጠና የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአምስት ዙር በሙያ ሥነምግባር፣ በሥነምግባር ምንነት፣ መርሆችና ፅንሰ ሀሳብ አተገባበር፣ የደንብ ማስከበር ስራዎች ለሙስና ያለው ተጋላጪነትና መከላከያ ስልቶች በሚሉ ርዕሶች ላይ ከ5 ሺ በላይ ለሚሆኑ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል።
ስልጠናው በዋናነት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተዘጋጅቶ ከተቋሙ ስራዎች ጋር በሚያያዙ የተለያዩ ርዕሶች ላይ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፥ ስልጠናው በመጠናቀቁ ዛሬ የመዝጊያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመዝጊያ መርሃ ግብሩ በስልጠናው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና የተሰጠ ሲሆን፥ የአዲስ አበባ የሥምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ላበረከተው አስተዋጽኦ በም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ አማካኝነት የእውቅና ሽልማቱን ተቀብለዋል። በመዝጊያ ፕሮግሙ የችግን ተከላ እና የተለያዩ ሁነቶች መከናወናቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
+ There are no comments
Add yours