የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አካሄዱ

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ረቂቅ ፖሊሲ ላይ የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ውይይት በማድረግ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ ታሳቢ ያደረገ ነው።

በመድረኩም ረቂቅ ፖሊሲው የቀረበ ሲሆን፥ የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለረቂቅ ፖሊሲው ግብዓት የሚሆን ሀሳብና አስተያየት በመስጠት ከመድረኩ ምላሸና ማብራሪያ ተሰጥቶበት የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡

You May Also Like

More From Author

+ There are no comments

Add yours