6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ አገር አቀፍ ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል አቅም ግንባታ ሥልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.መስከረም 8/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ) ኮሚሽኑ አገር አቀፍ ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል አቅም ግንባታ ሥልጠና ለሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ሊሰጥ ነው፡፡

ኮሚሽኑ አገር አቀፍ ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል አቅም ግንባታ ሥልጠና በየዘርፉ በሚፈጸሙ እና የመፈጸም ሥጋት ከፍተኛ እንደሆኑ በተለዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ከመስከረም 10/2015 ዓ.ም ጀምሮ በየዘርፉ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር መሠረት ለሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና አስፈጻሚዎች እና ባለሙያዎች ይሰጣል።

ስልጠናው እንደየዘርፉ ተጨባጭ ሁኔታ ሙስና እና ብልሹ አሠራር ያለበትን ደረጃ በቂ ግንዛቤ ይፈጠራል፤ እንዲሁም በየዘርፉ ከፌደራል እስከ ወረዳ መዋቅር የተመደቡ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና አስፈጻሚዎች እና ባለሙያዎች የትስስር ፎረም በመፍጠር የተቀላጠፈ የሙስና እና ብልሹ አሠራር መረጃ ልውውጥ እንዲያደርጉ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል።

ስልጠናው በ2015 በጀት ዓመት ጀምሮ ዘርፍ-ተኮር የሙስና እና ብልሹ አሠራር መከላከል ከፌደራል እስከ ወረዳ መዋቅር በመቀናጀት የሚከናወን ይሆናል፤ የሙሰኞችን የትስስር መረብ መበጣጠስም ቀዳሚ እርምጃው ይሆናል፡፡

በዚህም መሰረት ሕዝባችን እና ባለድርሻ አካላት የፀረ-ሙስና ትግል አጋርነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽናችን ጥሪዉን ያቀርባል።

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

መልካም አዲስ ዓመት!

Related Posts

Leave a Reply