6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሚያዚያ 4/2014 ዓ.ም ቢሾፍቱ):- የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቀጣይ ሦስት ወራት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው የ2014 በጀት ዓመት የፌደራልና የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀምን በገመገመበትና አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና የትስስር ጉባኤ ምስረታ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በጉባኤው ላይ ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንዳስታወቁት በቀጣይ ሦስት ወራት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ላይ አትኩሮ የሚሰራው በመላው አገሪቱ በተካሄደው የህዝብ ውይይት መድረክ በህዝብ ለተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡

በዘመቻ መልክ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን ይህን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ ግብረ-ኃይል እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡ ግብረ-ኃይሉና ኮሚቴዎቹ በኮሚሽነሮችና በምክትል ኮሚሽነሮች የሚመሩ ሲሆን ሌሎች የቴክኒክ ኮሚቴ አባላትም እንደሚኖሩ ተጠቁሟል፡፡

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

Related Posts

Leave a Reply