6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

በዲጂታል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች ተሰጠ፡፡

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ሚያዚያ 5/2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ):- በዲጂታል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች መሰጠቱ ተገለፀ፡፡

ሥልጠናውን የሰጡት በፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሀብት ምዝገባ ባለሙያ የሆኑት አቶ ግርማ አበበ እንደገለፁት ዲጂታል የሀብት ምዝገባው የመረጃ ጥራትን የሚጨምር፣ ተደራሽነትን የሚያሰፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ከዘመናዊ የዲጂታል አሠራር ጋር የሚጣጣም ነው፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት የነበረውን በሰነድ የታገዘ የሀብት ምዝገባ ወደ ዲጂታል በመቀየር ምዝገባ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም ይህንኑ ተከትሎ ለመላው አመራርና ሠራተኛው ስለ ዲጂታል ሀብት ምዝገባው ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደረገው ጥረት የሚያበረታታ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በሀብት ምዝገባው የሚንቀሳቀስ ሀብት፣ የማይንቀሳቀስ ሀብት፣ ልዩ ልዩ ገቢዎችንና ህጋዊ የሆኑ እዳዎች የሚመዘገቡ መሆኑም ተገልጿል፡

የህዝብ ተመራጮች፣ ተሿሚዎችና የመንግስት የልማት እና የህዝባዊ ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ሀብትና ንብረታቸውን እስከ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በዲጂታል እንዲያስመዘግቡ በገለፁ ይታወሳል፡፡

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

Related Posts

Leave a Reply