6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

አገር አቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ሚያዚያ 3/2014 ዓ.ም. አዳማ):- የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው አገር አቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የፌደራልና የክልል ኮሚሽነሮች በተገኙበት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡በጉባኤው የፌደራልና የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የ2014 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን ከሪፖርቱ በመነሳትም ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚመላከቱ ይጠበቃል፡፡አገር አቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤን መመስረት ሌላው በጉባኤው የሚዳሰስ አጀንዳ መሆኑም ታውቋል፡፡በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደገለፁት ሙስና የሚያስከትለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳት ከማስገንዘብ ባሻገር ወደ ተግባር በመግባት የሙስናና ብልሹ አሠራር ስጋት ጥናት በማካሄድ፣ በመለየትና በማጋለጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ጉባኤው ነገ ሚያዚያ 4 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቀጥል ይቀጥላል፡፡

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

Related Posts

Leave a Reply