6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. መጋቢት 30/2014 ዓ.ም. ቢሾፍቱ):- የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት አፈፃፀም የኮሚሽኑ ሠራተኞችና አመራሮች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ ገመገመ፡፡የኮሚሽኑ የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃፀም በዋነኛነት ያተኮረው በሥነምግባር አቅምና ብቃት ማሳደግ፣ በሙስና ስጋት ጥናትና ክትትል፣ በሙስና መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት እንዲሁም በተቋም አቅም ግንባታ ዙሪያ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ነው፡፡በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችን ይበልጥ ማጎልበት ድክመት የታየባቸውን አሠራሮች በጊዜው ማረምና በቀጣይ የተሻለ ውጤት በማከናወን ኮሚሽኑ ህዝብና መንግስት የሰጠውን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በግምገማው ወቅት አብራርተዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አያይዘውም በየሥራ ክፍሉ ለተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው በኮሚሽኑ የተጀመረው የለውጥ ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ በኮሚሽኑ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች የኮሚሽኑ የሥራ ሀላፊዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

Related Posts

Leave a Reply