6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

በኮሚሽኑ የተሰጠው የወንጀል ምርመራና ክስ ሥልጠና ክፍተቶችን የሚሞላ እንደነበረ ሰልጣኞች ተናገሩ፡፡

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. መጋቢት 30/2014 ዓ.ም. ቢሾፍቱ):- በሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ከፍትህ ተቋማት ለተውጣጡ አካላት የተሠጠው ሥልጠና የአሰራር ክፍተቶችን የሚሞላ እንደነበር በሥልጠናው የተሳተፉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ።በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ዳኛ አቶ ብሩክ አያሌው እንደተናገሩት ሥልጠናው የሙስና ወንጀል ባህርያትን እና የህግ አተረጓጎምን በዝርዝር ያሳየ በመሆኑ ተጨማሪ ግንዛቤን ፈጥሯል፡፡ ሥልጠናው በቀጣይም በየደረጃው ላሉ የፍትህ ተቋማት ሠራተኞች ተከታታይነት ባለው መልኩ ቢሰጥ በሥራ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ከፍትህ ሚኒስትር የሥነምግባር መከታተያ ክፍል የመጡት አቶ ዘርአይ ገ/ስላሴ በበበኩላቸው ሥልጠናው በአከራካሪ ሀሳቦች ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ገልፀው እንደዚህ አይነቱ ሥልጠና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡ከህብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል አሰራር መዘርጋትና ህፃናትም በሥነምግባር ታንፀው እንዲያድጉ የሚያግዝ ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል አማካሪ ወ/ሮ ገነት መኩሪያው ናቸው።

ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!

Related Posts

Leave a Reply