6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

በሙስና ወንጀሎች ምርመራና ክስ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሠጠ ነው።

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.፣ መጋቢት 28/2014 ዓ.ም. ቢሾፍቱ)፡- በሙስና ወንጀሎች ምርመራና ክስ ላይ የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው ስልጠና ከክልሎች፣ ከከተማ አስተዳደሮችና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አካላት በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ እየተሰጠ ነው።በስልጠናው ላይ በአስሩ ክልሎች ከሚገኙ ጠቅላይ ፍ/ቤቶች፣ ጠቅላይ ዐቃቢያነ ህግ፣ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች፣ ከፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ዘርፍ፣ ከፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ዘርፍ፣ ከማረሚያ ቤቶች፣ ከፌደራል ፍ/ቤቶች፣ ከአዲስ አበባና ድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖችና ከፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ክፍል የተውጣጡ ሠልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።ስልጠናው የሙስና ወንጀሎች፣ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ፣ የሙስና ወንጀሎች ክስ እና የሙያ ሥነ-ምግባር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከመጋቢት 28-30/2014 ዓ.ም. የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

Related Posts

Leave a Reply