6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙስና ሥጋት ጥናት ለማካሄድ ከ200 በላይ የጥናት ቡድን አባላትን ሊያሠማራ ነው፡፡

(ፌ.ሥ.ፀ.ኮ. መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ቢሾፍቱ ) ፡- የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ በትምህርት፣ በገቢ እና ፍርድ ቤቶች ላይ የሙስና ሥጋት ጥናት ለማካሄድ ከ200 በላይ የጥናት ቡድን አባላትን አሰማራ፡፡ኮሚሽኑ ከፌደራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የጥናት ቡድን አባላት የሙስና ሥጋት ጥናት ንድፈ-ሀሳብ በማዘጋጀት በዘርፉ ምሁራን ከመጋቢት 15-18 ቀን 2014 ዓ.ም ለአራት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡በሥልጠናው ማጠቃለያና በጥናት ሥራው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደገለፁት በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ የሙስና ሥጋት ጥናት ከተካሄደ በኋላ ጥናቱን መነሻ በማድረግ ተቋማት በየዘርፋቸው የሙስና መከላከል ስትራቴጂ አዘጋጅተው እንዲተገብሩ ይደረጋል፡፡ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሥልጠናው ጥናቱን በብቃት ለማከናወን ከፍተኛ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀው በተቋማት የሚስተዋሉ የሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ለይቶ ለመከላከል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

Related Posts

Leave a Reply