6133 0115533852 / 0935947533Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

House of Peoples Representatives of FDRE

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሙስናን ለመታገል የክትትልና የቁጥጥር ሥራውን በማጠናከር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታወቀ፤
(ዜና ፓርላማ)፣ ህዳር 23/ 2014 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ኩባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ም/ቤት ሙስናን ለመታገል የክትትልና የቁጥጥር ሥራውን በማጠናከር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
አፈ ጉባኤዋ ይህን ያሉት ህዳር 30 በሃገር አቀፍ ለ17ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ- ሙስና ቀን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
ከለውጡ በፊት በትልልቅ አገራዊ ፕሮክቶች ሲደረስ የነበረውን የሙስና ምዘበራና የአገሪቷ ስልጣን በተወሰኑ ቡድኖች እጅ በመውደቁ ህዝቡ ለስደት፤ ለእንግልት ለተለያዩ ስቃዮች ሲጋለጥ እንደነበር አስታውሰው፤ ከብልሹ አሰራር በመውጣት ህዝቡ አገልግሎት ማግኘት ያለበት በገንዘብ ሳይሆን በነጻ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ጠቆመዋል፡፡